ፖለቲካዊ አደረጃጀትና አስተዳደራዊ መዋቅር

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት ሕገ-መንግስታዊ አወቃቀርን ተከትሎ በሦስቱ የመንግሥት አካላት ማለትም በሕግ አውጭው፣ በሕግ አስፈፃሚውና የዳኝነት አካላት የተዋቀረ ነዉ፡፡ ክልሉን ከሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች የተለየ የሚያደርገዉ በሁለት ምክር ቤቶች የተዋቀረ መሆኑ ነዉ፡፡ እነሱም የሕግ አውጪ አካል የሆነው የክልል ምክር ቤት እና ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሚወከሉበት የክልሉ የብሔረሰቦች ም/ቤት ናቸዉ፡፡ አስፈፃሚው የመስተዳድር ምክር ቤት በርዕሰ መስተዳድሩ የሚመራ ሲሆን የዳኝነት አካሉ በጠቅላይ ፍ/ቤት ኘሬዝደንት ይመራል፡፡ ይህ አደረጃጀት ከክልሉ ብሔረሰቦች ም/ቤት በስተቀር በተዋረድ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ 14 ዞኖች እና 4 ልዩ ወረዳዎች ተዘርግቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ፡፡