ማኀበራዊ ሁኔታዎች

በማህበራዊ ዘርፍ በ2ዐዐ7 ዓ.ም. የመዋዕለ ሕጻናት ትምህርት ቤቶች ብዛት 642፣ የ1ኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሳይክል ትምህርት ቤቶች ብዛት ወደ 6227 አድጓል፡፡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብዛት ደግሞ 641 ያህል ደርሰዋል፡፡ የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆችን በተመለከተ 5 ኮሌጆች ተገንብተዉ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠናን በተመለከተ በዚህ ዘርፍ በክልሉ 44 የመንግሥትና 12 የመያድ ተቋማት ይገኛሉ፡፡ በክልሉ ውስጥ 7 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በክልሉ ርዕሰ ከተማና በተለያዩ ዞኖች፣ ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ በጤናው ዘርፍ በ2ዐዐ7 ዓ.ም. የጤና ኬላ አገልግሎት ሽፋን 100% የደረሰ ሲሆን፣ የጤና ጣቢያዎች አገልግሎት 95% (719 በቁጥር) ደርሷል፤የሆስፒታሎች ቁጥር ደግሞ 24 ከነበሩት ነባር ሆስፒታሎች 31 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ግንባታ ተጠናቋል፡፡ በተጨማሪም 19 የመካከለኛ ደረጃ ሆስፒታሎች ግንባታ ተጀምሮ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡